ባለፈው ሳምንት የተደረገውን የስራ ማቆም አድማ ተሳትፋችሁዋል የተባሉ የህሊና ምግብ ፋብሪካ ሰራተኞች ቅዳሜና እሁድ ያለ ክፍያ እንዲሰሩ ታዘዙ
(ኢሳት ዜና የካቲት 30 ቀን 2010 ዓ/ም) ለገጣፎ የሚገኘው ህሊና የተመጣጠነ ምግብ አምራች ኩባንያ ባወጣው ማስጠንቀቂያ ሰራተኞች ያለ ምንም ክፍያ ቅዳሜ እና እሁድ እየገቡ የማካካሻ ስራ እንዲሰሩ ታዘዋል። ድርርጅት ከዚህ በሁዋላ ሰራተኞች በስራ ማቆም አድማ የሚሳተፉ ከሆነ ያለ ምንም እረፍት ከ4-5 ወራት እንደሚሰሩ ተነግሯቸዋል።
ኩባንያው በስብሰባ አዳራሹና በእንግዳ ማረፊያ ክፍሉ የቀድሞውን ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ፎቶ ግራፍ ለጥፎ እንደሚገኝ እንዲሁም የኩባንያው ማኔጅመንት ከኢህአዴግ ባለስልጣናት ጋር የጠበቀ ግንኙት እንዳላቸው ምንጮች ገልጸዋል። “ብሌስ አግሪ ፉድ” የተባለ እህት ኩባንያ ሲከፈት ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረ ሚካኤል በእንግድነት ተገኝተው መርቀውታል። በኦሮምያ የሚካሄደው የስራ ማቆም አድማ በአገዛዙ ላይ የኢኮኖሚ ጫና ለመፍጠር መሆኑ እየታወቀ እንዲህ አይነት አገዛዙን የሚደግፍ እርምጃ መውሰዱ ሰራተኞችን አስቆጥቷል።