ለ 95 ክፍት የስራ ቦታ 13 ሺ ሰዎች አመለከቱ
(ኢሳት ዜና የካቲት 21 ቀን 2010 ዓ/ም) የአዲስ አበባ ከተማ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን 95 ባለሙያዎችን ለመቅጠር ላወጣው ማስታወቂያ 13 ሺ ተወዳዳሪዎች ማመልከታቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።
ባለሥልጣኑ ታኅሳስ 15 ቀን 2010 ዓ.ም 95 ሰራተኞችን ለመቅጠር ያወጣውን ማስታወቂያ ተከትሎ ስራ ፈላጊዎች የባለሥልጣኑ ዋና መሥሪያ ቤት አጥለቅለቀው ሰንብተዋል ብሎአል ጋዜጣው።
መስሪያ ቤቱ እንዲህ አይነት ብዛት ያለው ስራ አመልካች ሲመጣ ያልተለመደ