የነቀምት ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

የነቀምት ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
(ኢሳት ዜና የካቲት 19 ቀን 2010 ዓ/ም) በኦሮምያ ክልል በወለጋ ነቀምት ህዝቡ ወደ አደባባይ በመውጣት የተቃውሞ ሰልፍ አድርጓል። በተቃውሞ ሰልፉ ላይ በአካባቢያቸው የተሰማሩት ወታደሮች ለቀው እንዲወጡ ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲሰረዝ በአጠቀላይ አገዛዙን የሚያወግዙ መፍክሮች ተሰምተዋል።
የአጋዚ ወታደሮች በህዝቡ ላይ የተኮሱ ሲሆን፣ ጉዳት መድረሱና አለመድረሱ የታወቀ ነገር የለም። በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ከህዝቡ ጋር ለመነጋገር ቀደ ነቀምት ሲጓዙ መንገድ ላይ በወታደሮች በመታገታቸው ውዝግብ ተፈጥሮ የነበረ ሲሆን፣ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎቹወደ ከተማ ለመግባት የነበራቸውን እቅድ በመሰረዛቸው ግጭት እንዳይፈጠር ለማድረግ ችለው ነበር። በአገዛ ወታደሮች ድረጊት የተበሳጨው ህዝብ ዛሬ ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞውን ሲያሰማ ውሎአል።