በግብጽ በ21 ተከሣሾች ላይ የሞት ፍርድ ተላለፈ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 15/2010)

የግብፅ ፍ/ቤት በ21 ተከሣሾች ላይ በዛሬው ዕለት ሞት ፈረደ፤

ፋይል

የሐገሪቱን የሙስሊምች መንፈሣዊ መሪ ዕውቅና ያገኘው ይህ የሞት ፍርድ የተላለፈባቸው 21 ተከሣሾች እ/ኤ/አ/ 2015   በባህር ዳርቻዋ ከተማ ዳማይታ ፖሊስ ጣቢያ  ላይ እንዲሁም በነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ ላይ የሽብር ጥቃት  በማድረስ የተወነጀሉ ናቸው።

የግብፅ ፍ/ቤት በዛሬው ዕለት የሞት ፍርድ ካሣለፈባቸው 21 ተከሣሾች 16ቱ በሌሉበት ውሣኔ እንደተላለፈባቸው ታውቋል፡፡ሌሎች 4 ተከሣሾች የ25 ዓመታት እሥራት ሲፈረድባቸው -:ሦስቱ ደግሞ 15 ዓመታት ተፈርዶባቸዋል.::

የቀድሞው የግብፅ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ በሕዝብ ግፊት ሥልጣናቸውን ከለቀቁ በኋላ ሙሐመድ ሙርሲ በግብፅ ታሪክ የመጀመሪያው በሕዝብ የተመረጡ መሪ መሆናቸው ይታወቃል፡።

በጄኔራል አብዱልፈታህ አል ሲሲ በተመራ መፈንቅለ መንግስት መሐመድ ሙርሲ ተባረው እስር ቤት ከገቡ ወደህ የሽብር እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል፤

የግብፅ ፍ/ቤቶች ተከታታይ የሞት ፍርድ ውሣ ኔም የሽብር ድርጊቱን አልገታውም፡፡የአዉሮፓ ሕብረት በግብፅ ፍ/ቤቶች እየተላለፈ ያለው ተከታታይ የሞት ፍርድ እንዳሣሠበው በዚህ ወር መጀመሪያ መግለፁንም መረዳት ተችሏል፡፡