በኦሮሚያ የተጠራው በቤት ውስጥ የመቀመጥና የስራ ማቆም አድማ እንደቀጠለ ነው

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 6/2010)

በኦሮሚያ ክልል የተጠራው በቤት ውስጥ የመቀመጥና የስራ ማቆም አድማ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሏል።

ትላንት ያልተሳተፉ ከተሞች ዛሬ ተቀላቅለዋል።

በጅማ ሁለት የሰላም ባስ አውቶቡሶች መቃጠላቸውን የደረሰን መረጃ ያስረዳል።

በፍቼ የአጋዚ ወታደሮች በአንድ ትምህርት ቤት ላይ በወሰዱት ርምጃ አራት ተማሪዎች ክፉኛ ተጎድተዋል።

በደብረዘይትና ጅማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ አደባባይ በመውጣት በስልጣን ላይ ያለውን ስርአት አውግዟል።

ከምዕራብ ሃረርጌ አሰቦት-ጭሮ-መኢሶ አብዛኞቹ ከተሞች አድማውን መተዋል።

በአዲስ አበባ ዙሪያ አድማና የተቃውሞ ሰልፍ ሲደረግ መዋሉም ታውቋል።