በባህርዳር የባለስልጣናት ንብረት እንደሆኑ የሚታመኑ ሆቴሎች ልዩ ጥበቃ እየተደረገላቸው ነው

(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 22/2009)በባህርዳር የባልስልጣናት ንብረት እንደሆኑ የሚታመኑ ሆቴሎች የተለየ ጥበቃ እንደተጀመረላቸው ተገለጸ።

የህውሃትና ብአዴን ባለስልጣናት በጀርባ በባለቤትነት የያዝዋቸው ሆቴሎች ጥቃት ሊደርስባቸው ይችላል በሚል በፌደራልና በልዩ ሃይል እየተጠበቁ መሆኑን ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

የአቶ አዲሱ ለገስ ፓፒረስ፣ የአቶ በረከት ስምዖን ራይ ናይል እንዲሁም የአቶ አያሌው ጎበዜ ጋሳ ሆቴሎች ጥበቃ እየተደረገላቸው ከሚገኙ ሆቴሎች የሚጠቀሱ ናቸው።

በሌላ በኩል በባህርዳር አንድ የደህንነት አባል ተገድሎ ተገኝቷል።

በደብረታቦር አድማ አልሳተፍም ባለ የስርዓቱ ደጋፊ ባለሀብት ንብረት ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጿል።