(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 27/2009) የግብር መክፈያው የጊዜ ገደብ ሐምሌ 30 እየተቃረበ ቢመጣም በአብዛኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች የንግዱ ማህበረሰብ የተጣለበትን የቀን ገቢ ግብር እየከፈለ እንዳልሆነ የደረሰን መረጃ አመለከተ።
በአብዛኛው የአማራ ክልል ከተሞች ነጋዴው ግብር እንደማይከፍል በማስታወቁ የመንግስት ሃላፊዎች ስለሚወስዱት እርምጃ ግራ እንደተጋቡ ተገልጿል።
በሸዋ ሮቢት ለ4ኛ ቀን አድማው በቀጠለበት በዛሬው እለት ተሳትፈዋል የተባሉ የንግድ ቤቶች በመታሸግ ላይ ናቸው።
በደብረታቦር ቤት ለቤት ቅስቀሳ በማድረግ ህዝቡ ወቶ እንዲከፍል እየተለመነ ነው
በኦሮሚያ እስከ ነሀሴ 15 የግብር መክፈያ ጊዜው የተራዘም ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎች አሁንም የንግድ ቦታዎች ስራ አልጀመሩም
በአዊ ዞን ዚገም ወረዳ ጎሃ ቀበሌ በበርበሬ ንግድ የተሰማሩ ነጋዴዎች በዘፈቀደ የተወሰነብንን ግብር እንከፍልም በማለት የንግድ ፈቃዳቸውን መመለሳቸውም ታውቋል።