ደቡብ ሱዳን 14 ዳኞችን ከስራ አባረረች

 

 (ኢሳት ዜና– ሐምሌ 7/2009)የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ከስልጣን የሚያባርሩት አመራር እየተበራከተ መቷል ይላል የሀገሪቱ የዜና ኮርፖሬሽኝ በዘገባው።

ምናልባትም ሳልቫኪር ለመንግስታቸው ስጋት ናቸው ያሏቸውን ብሎም ከተቃዋሚ ሃይል ጋር ግንኙነት ሊኖራቸው ይችላል በሚል ፓርቲያቸው ጥርጣሬ ከገባው ያለምንም ምክንያት ባለስልጣናቱን ከቦታቸው ለማባረር ወደ ኋላ አይሉም ሲል ዘገባው ያክላል።

ለዚህም ማሳያ አድርጎ የሚያቀርበው የሃገሪቱ የጦር አዛዥ የነበሩት ጄምስ ሆዝ ማይና የተለያዩ የፖሊስ ከፍተኛ ጄነራሎችን  እንዲሁም በሀገሪቱ ቁልፍ ቦታ የነበራቸውን የፖሊስ አዛዥ በተለያየ ጊዜ ማባረራቸውን ነው።

ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ባለስልጣናቱን ሲያባርሩ ደግም ለምን ተባርሩ ለሚለው ምንም አይነት ምክንያት አያስቀምጡም።

አሁንም በፕሬዝዳንቱ ትእዛዝ 14 ዳኞች ከስልጣናቸው ተባረዋል።     ሁለቱ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች፣አምስቱ ደግሞ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች ሲሆኑ ሁለቱ ደግሞ የሁለተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ናቸው።

ዳኞቹ ስለተባረሩበት ምክንያት ፕሬዝዳንቱም ሆኑ ጽህፈት ቤታቸው እንዲሁም የሀገሪቱ የፍትህ ሚኒስትር ያሉት ነገር የለም።

በዳኞቹ ላይ ውሳኔው የተላለፈው በዳኞቹና በፕሬዝዳንቱ በተቋቋመው ኮሚቴ መካከል ሲካሄድ የነበረው ውይይት ያለ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው።

የተባረሩት ዳኞች በሀገሪቱ ያለው የአስራር ሂድት ሊሻሻል ይገባል በሚል ዘመቻ ሲያካሂዱ እንደነበር ታውቋል።

ውይይቱ በዋናነት ዳኞቹ ባቀረቡት የመብት ጥያቄ ላይ ያተኮረ ነበር።

የዳኞቹ ሊቀመንበርና የፍትህ ኮሚቴ የሆኑት ካሊድ አብዱላ ሞሃመድና ሌሎች የስራ ባልደረቦቻቸው ከፍተኛ የሆነ የደሞዝ ጭማሪ ሊደረግ ይገባል የባልደረቦቻችን ከስራ መባረርም የህግ ስርአቱን ይጎዳዋል ሲሉ ተቃውሞ አሰምተዋል።