ሐምሌ ፮ ( ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወጣት ታዲዮስ በምርጫ 97 ወቅት በቅንጅት ውስጥ ታቅፎ አዲስ አበባ ወጣቶችን በማደረጀትና በመምራት ከፍተኛ ሚና የተጫወተ ሲሆን፣ የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ በወቅቱ ካሰራቸው ወጣት የቅንጅ አመራሮች መካከል አንዱ ነበር።
ወጣት ታዲዮስ በእስር ቤት ውስጥ ለ2 አመታት ያክል ታስሮ ከተፈታ በሁዋላ ወደ አውስትራሊያ ተሰዶ ፣ በነጻነት ትግሉ ውስጥ አስተዋጽኦ ሲያካሂድ ቆይቷል። በጓደኞቹ ዘንድ በትህትናውና በችሎታው የሚወሳው ታዲዮስ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።
ኢሳት በወጣት ታዲዮስ ሞት የተሰማውን ሃዘን እየገለጸ፣ ለቤተሰቦቹና ለጓደኞቹ መጽናናትን ይመኛል።