ሰኔ 28/2009
የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥንና ሬድዮ የተመሰረተበት 7ኛ ግምት በቴነሲ ግዛት ናሽቪል ከተማ ተከበረ ። በከተማዋ የሚገኙ የኢሳት ደጋፌዎች በተገኙበትና በሳምንቱ መጨረሻ በተካሄደው መድረክ ኢሳትንና የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮችን የተመለከቱ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ውይይትም ተካሂዷል ።
የናሽቪል የኢሳት ኮሚቴ ባዘጋጀውና ቅዳሜ ጁላይ 2/20/17 በተካሄደው ዝግጅት ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና እንዲሁም ኮሜዲያን ክበበው ገዳ የተገኙ ሲሆን ከአጎራባቿ ከተማ ሜንፈስ የመጡ የኢሳት ደጋፊዎችና በዝግጅቱ በመታደም ከፍተኛ የገንዘብ መዋጮ አድርገዋል ፤ ለጨረታ የተዘጋጀውንም ስጦታ አሸንፈው ወስደዋል ።
በኢሳት ዙሪያ በርካታ ጥያቄዎች የተነሱበትና ውይይት የተካሄደበት የናሽቪል የኢሳት 7ኛ አመት ዝግጅት በጨረታና በትኬት ሽያጭ ለኢሳት ማጠናከሪያ ገንዘብ ተሰብስቧል ። ለጫረታ የቀረበው የኢሳትን 7ኛ አመት የሚያንጸባርቅና በኢትዮጵያ ሰንደቅአላማ ያሸበረቀ ስጦታ በ 10,000 የአሜሪን ዶላር መሸጡንም ለመረዳት ተችሏል ።ይህ በእንዲህ እንዳለም የኢሳት 7ኛ አምት በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች አሁንም ቀጥሏል ። በነገው እለት ሃሙስ ጁላይ 6/2017 የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን አመታዊ ዝግጅት በሚያካሄድበት ሲያትል ከተማ የኢሳት 7ኛ አመት የሚከበር ሲሆን የኢሳት ባልደረቦችም ከዋሽንግተን ዲሲ ተሳታፊዎች መሆናቸውን ከወጣው መረሃ ግብር መረዳት ተችሏል ። በቀጣዩ ሳምንት ጁላይ 15 ኣና 16 ቅዳሜና እሁድ በሳሆዜና ሳንዲያጎ የኢሳት 7ኛ አመት በተመሳሳይ ይከበራል ።