በሃረር በተጀመረው የዲያስፖራ ቀን በአል የመንግስት መስሪያ ቤቶች እንዲዘጉ በመደረጉ ህዝቡ ሲጉላላ ዋለ

ሰኔ ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ዘጋቢያችን እንደገለጸው ዛሬ ረቡዕ በተጀመረው የዲያስፖራ ቀን በአል ላይ ፕሬዚዳንቱ ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ እና አቶ አባይ ጸሃየ የተገኙ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቶችን ጨምሮ አጠቃላይ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በመዘጋታቸው ህብረተሰቡ አገልግሎት ለማግኘት ሲንገላታ ውሎአል። መረጃዎቸ እንደሚያሳዩት አጠቃላይ የዝግጅቱን ሃላፊነት የወሰዱት ከህወሃት ጋር ግንኙነት ያላቸው ኩባንያዎች ናቸው።
አጠቃላይ ዝግጅቱ ለአንድ ወር እንደሚቆይ ታውቋል።
የከተማው ህዝብ ወደ ዝግጅቱ ቦታ የሚወስዱ መንገዶች በመዘጋታቸው ሲጉላላ መዋሉንም ዘጋቢያችን ገልጿል።