34ኛ አመት ያስቆጠረው የሰሜን አሜሪካ የስፖርት ፌደሬሽን ዠግጅት እሁድ July 2, 20172 በዋሽንግተን ሲያትል ሬንተን ስቴድየም ብዙ ሺህ ተመልካቶች በተገኙበት ከወትሮው በተለየ ሁኔታ መጀመሩን በስፍራው የተገኘው የኢሳት ጋዜጠኛ ተወልደ በየነ ዘግቧል።
በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌደሬሽን ለ34ኛ ጊዜ በአሜሪካ ሲያትል ያዘጋጀው አመታዊ ስነ-ስርአት ከወትሮ በተለየ ሁኔታ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ታዳሚ ተገኝቶበታል። የኢትዮጵያ ባህልና ወግ የተንጸባረቀበት ስነ-ስርአቱ የተከበረው በሬንተን ስቴድየም ከመሆኑ ሌላ የዘንድሮውን ዝግጅት በአለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቀው የትራንስፖርት ኩባንያም ስፖንሰር አድርጎታል። በሄሊኮብተሮች ታጅቦ በኢትዮጵያ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ አላማ በማውብለብለብ የተጀመረው ይህ ዝግጅት እጅግ ደማቅ እንደሆነ በስፍራው የተገኘው ዘጋቢያችን ተወልደ በየነ ዘግቧል።
የስነ–ስር አቱ የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ተስፋዬ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል።
እንደ አቶ ጌታቸው ገለጻ ኢትዮጵያውያን የሚታደሙበትና ለሃገር ያላቸውን ፍቅር የሚገልጹበት አመታዊው የፌደሬሽኑዝግጅት በእጅጉ እየተጠናከረ መጥቷል።
ይህን በሁሉም ዘንድ የሚወደደውን የኢትዮጵያውያን የህብረት፣ የአንድነትና የፍቅር መግለጫ ለማዳከም በሼህ መሃመድ አላሙዲን የበጀት ደጋፊነት ተቋቁሞ የነበረው ተመሳሳይ ዝግጅት ተዳክሞ ከሂደቱ መውጣቱንም አስታውሰዋል።
ለዚህ ሁኔታ ለመብቃት አስተዋጽዎ ያደረጉትን በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንንም አመስግነዋል። በሲያትል በተጀመረው የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌደሬሽን ሁለት የእግር ኳስ ቡድኖች ሳንዲያጎና ኢትዮዳላስ ተጫውተው 2 ለ 2 ተለያይተዋል።