የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የሚያቀርባቸው ሪፖርቶች በሃሰት ላይ የተመሰረቱ መሆናቸው ተገለጸ

የኢህአዴግ ፓርላማ የመንግስት ልማት ድርጅት ቋሚ ኮሚቴ አባላት የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ)  የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አቀራረቡ  ያልሰራውን እንደሰራ አድርጎ ሰለሆነ የተሳሳተ መረጃ እንደመስጠት ተደርጎ ሊቆጠር እንደሚገባ ተናግረዋል

የፓርላማው ተወካዮች እንደገለጹት ሜቴክ ከአቅሙ በላይ የሆኑ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በመረከብ ለተራዘሙ አመታት በመንጓተቱ የሃገሪቱ የፋይናንስ ስርአትን ባልተከተለ ሁኔታ ገንዘብ ማባከኑ፤ የፕሮጀክት ባለቤቶች ከሆኑ መንግስታዊ ተቋማት ጋር ጤናማ ግንኙነት መፍጠር አለመቻሉ በተለያዩ አካላት ችግሮቹን እንዲያስተካክል ቢነገረውም ለማሻሻል ፍላጎት አለማሳየቱ በአጠቃላይ የአመራር ችሎታና ብቃት የሌለው ተቋም በመሆኑ ተጠያቂ ሊሆን እንደሚገባም አስታውቀዋል

የሜቴክ የበላይ ሃላፊ የሆኑት የህውሃት የጦር ጀኔራሎች የውሸት ሪፖርት ያቀርባሉ በማለት በአብነት ከተነሱት ውስጥ የጣና በለስ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክት አፈጻጸም 25 በመቶ መሆኑ እየታወቀ ሜቴክ 57 በመቶ አጠናቅቄላሁ ማለቱ የያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ አፈጻጸሙ 46 በመቶ ቢሆንም ሜቴክ 60 በመቶ ክፍያ መቀበሉ  ኦሞ ኩራዝ አንድ ፋብሪካ ሜቴክ አጠናቅቄላሁ ብሎ ቢገልጽም የፕሮጀክቱ ባለቤት 94 በመቶ በታች እንደተፈጸመ መግለጻቸውን በምሳሌነት ተነስቷል

ለቀረበባቸው የአመራር አቅም ማነስና ችሎታ ማጣት የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውበግሌ የማምነው ለዚህ ሃገር ልማት እየወደቅንና እየተሰዋን እንደምንሰራ ነው ’  በማለት ሜቴክ እየቀረበበት ካለው ተጨባጭ ችግር የማይያያዝና ማስፈራሪያ ያዘለ ምላሽ ሰጥተዋል