ኢሳት (ሰኔ 23 ፥ 2009)
የኤርትራ መንግስት ወደ አለም አቀፍ መድረክ እየተመለሰ መምጣቱና የገንዘብ ድጋፍ እያገኘ መሄዱ ለኢትዮጵያ መንግስት ስጋት መደቀኑን የአሜሪካውያኑ የትንተና መጽሄት ፎርየን ፖሊሲ ዘገበ። The Rehabilitation of Africa’s most isolated dictators በሚል ርእስ መጽሄቱ ባሰፈረው ሰፊ ዘገባ ኤርትራ ከመከላከኛው ምስራቅ ሃገሮች ባሻገር ከምእራብያውያን ጋርም ግኑኝነቷን ተንትኗል።
በየመን የተፈጠረውን ቀውስ ተከትሎ ከሳውዲ አረቢያና ከተባበሩት አረብ ኤምሬት ጋር የፈጠረችውን ትብብርና ያገኘችውን ድጋፍ የሚዘረዝረው ታዋቂው የትንተና መጽሔት በዚህም የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዋሚዎችን ታጠናክርበታለች የሚል ስጋት በኢትዮጵያ በኩል መኖሩን ዘግቧል። በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣናት ጭምር መጎብኘት የጀመረችው ኤርትራ የኦባማ ከስልጣን መውረድ በተለይም የአምባሳደር ሱዛን ራይስ መገለል ከፍተኛ እፎይታ እንደሆናትም መጽሔቱ አብራርቷል።