በሙስና ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ መላኩ ፋንታ በጸና ታመዋል

ሰኔ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሙስና ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሥራ አስኪያጅ አቶ መላኩ ፋንታ በጸና መታመማቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል።
ጥቅምት ወር፣ 2006 ዓም በከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ መላኩ፣ በተከሰሱበት ወንጀል እንዲከላከሉ ባለፈው የካቲት ወር ፍርድ ቤቱ ብይን መስጠቱ ይታወቃል። አቶ መላኩ ምንም አይነት የሙስና ወንጀል አለመፈጸማቸውን ይናገራሉ።