ኢሳት (ግንቦት 14 ፥ 2009)
የአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ምርጫን በተመለከከተ በጄኔቭ በሚካሄደው ጉባዔ አዳራሽ በዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ላይ ተቃውሞ ቀረበ።
ማክሰኞ በጉባዔው መክፈቻ ላይ ጋዜጠኞች ከሚቀመጥበት ሰገነት የተሰማውን ተቃውሞ በአዳራሽ የነበሩ ጋዜጠኛ ወዲያውኑ በማህበራዊ መድረክ ያሰራጩት ሲሆን፣ ተቃውሞውን ያሰማው ኢትዮጵያዊ አቶ ዘላለም ተሰማ ከአዳራሹ እንዲወጣ ተደርጓል።
“ቴዎድሮስ ለአለም ጤና ድርጅት አይገባም አፍሪካውያን ደጋግማችሁ አስቡ” በማለት በጸጥታ ሃይላት በተያዘበት ወቅት ጭምር ተቃውሞን የቀጠለው አቶ ዘላለም ተሰማ፣ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃንሞ እንዳይመረጡ ኢትዮጵያውያን የጥረቱ ዘመቻ አካል እንደሆነም ተመልክቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም እንዳይመረጡ በመቃወም ከአዳራሹ ውጭ የተቃውሞ ሰልፍ እየተካሄደ ሲሆን፣ የመንግስት ደጋፊዎች በተመሳሳይ ሰልፍ ጠርተዋል።