ግንቦት ፫ ( ሦስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንዳደረሱን መረጃ በርካታ ወጣቶችን ሲገድልና ጠቁሞ ሲያስገድል በነበረው አበራ ቡልቻ ላይ የግድያ እርምጃ የተወሰደው በትናንትናው ዕለት ነው።
አበራ ቡልቻ የህወኃት- ኦህዴድ ተላላኪ በመሆን ከደላቸውና ካስገደላቸው የከተማው ወጣቶች መካከል ወጣት ኢያሱ ሰሎሞን ይገኝበታል። ስውር ሕዝባዊ ግብረ-ኃይሉ ትናንት በወሰደው በዚህ እርምጃ አበራ ቡልቻ ከመገደሉም ባሻገር የግብር ተባባሪው የሆነው ወንድሙ ክፉኛ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰበት ታውቋል።
በኦሮሚያ ክልል በሕዝባዊ አመጹ ጊዜ ወጣቶችን ሲገድሉና ሲያስገድሉ በነበሩ ደህንነቶችና ተላላኪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ትናንት የተገደለው አበራ ቡልቻ ባለፈው አንድ ወር ውስጥ እርምጃ የተወሰደበት ሦስተኛው የደህንነት አባል ነው።