ሚያዝያ ፳፭ ( ሃያ አምስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሃገራችን ካለችበት አደገኛ የሆነ የጥፋት አዘቅት ውስጥ እንድትወጣም ሆነ ፤የስርዓት ለውጥም መምጣት የሚቻለው እያንዳንዱ ዜጋ በተደራጀ መልኩ ሲታገል ፤ድርጅቶችም ሳይጠላለፉ በመመካከር ስራዎችን በጋራ መስራት ሲችሉ መሆኑን በውይይቱ ላይ ተነስቷል።
የትብብር መድረኩ በጀርመን አካባቢ የሚጠሩ ማናቸውም ሰላማዊ ሰልፎችና የተቃዋሚ እንቅስቃሴዎች በታቻለ መጠን በተቀናጀና በተናበበ መልኩ በጋራ እንዲዘጋጁ፣ በአካባቢው የሚካሄዱ የፖለቲካ ትግሎች የጎንዮሽ መሆኑ ቀርቶ የጋራ ጠላት በሆነው ወያኔ ላይ ማተኮር እንዳለበት ፣ እንዲሁም የተቃዋሚ ድርጅቶች መጠላለፍ አቁመው ተባብረውና ተከባብረው እንዲሰሩ፣ በአካባቢው ባሉ የእምነት ተቋሟት መሃከል ያሉ አለመግባባቶችን በሽምግልና ለመፍታት እንዲሞክሩ መክሯል
የወጣቶችና የሴቶችን ተሳትፎ ለማጎልበት ተገቢ ትኩረት መስጠት እንዲሁም በየአካባቢው የተሰገሰጉ ከፋፋይ የሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላቶችንና የወያኔ ሰላዮችን በአደባባይ መታገልና ማጋለጥ እንደሚገባም በውይይቱ ወቅት ተነስቷል።
እኤአ ሚያዚያ 29 ቀን 2017 በጀርመን የኢትዮጵያዊያን የውይይት ትብብር መድረክ በተዘጋጀው ስብሰባ ላይ ሊቀመንበሩ አቶ ጌታሁን አሰፋ የውይይትና የትብብር መድረኩን የሁለት ዓመታት የስራ ሪፖርት ለተሰብሳቢው አቅርበዋል።