ሚያዝያ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በይርጋለም ከተማ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ለአባይ ግድብ ግንባታ በግዳጅ እንዲያወጡ መጠየቃቸውን ከተቃወሙ በሁዋላ፣ ዛሬ አርብ ደግሞ የይርጋለም መምህራን ለግድቡ እንዲያዋጡ የተጠየቁ ቢሆንም፣ መምህራን ተቃውመውታል።
“መምህራኑ እኛ ያለን ዲግሪ ነው፣ ወረቀት ነው፣ ለራሳችን የሚሆን ፍጆታም የለንም” በማለት ተቃውመውታል። የካቢኔ ስብሰባ ላይ “የመንግስት ባለስልጣናትን ልብሳቸውንና ሰውነታቸውን ብታዩት ደረጃውን የጠበቀ ነው፣ ማሰብ ግን አይችሉም” ያሉት መምህራኑ፣ መምህሩ እየኖረ አይደለም፣ መንግስት ይህን ያውቃል፣ ማስተካከል ግን አልቻለም” ብለዋል።
“ ሰው እየኖረ እንጅ እየሞተ መስጠት አይችልምና እኛም ልጆቻችንም እንዳንሞት ጥንቃቄ ይደረግልን”፣ ያሉት መምህራኑ፣ በግድ ክፈሉ የምንባል ከሆነ ግን ሌሎች አማራጮች ይታዩልን ብለዋል።