የሰብአዊ ኮሚሽን ሪፖርትን ተከትሎ አመጽ ይነሳል በሚል በኦሮምያ የፌደራል ፖሊሶች ተሰማሩ

ሚያዝያ ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቀደሞው ምርጫ ቦርድ ም/ል ሰብሳቢ በህወሃቱ አባል ዶ/ር አዲሱ ገ/እግዚአብሄር የሚመራው ራሱን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ብሎ የሚጠራው ድርጀት ከፍተኛ አመጽ ተነስቶባቸው በነበሩ የኦሮምያ ከተሞች 495 ሲቪል ዜጎች መገደላቸውን ይፋ ካደረገ በሁዋላ፣ ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቀሴ በድጋሜ ሊጀመር ይችላል በሚል በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላትን ወደ አካባቢው ልኳል።
በደንብ የታጠቁ ወታደሮች የአመጹ ማእከል ናቸው ተብሎ ወደ ሚታመንባቸው አካባቢዎች መንቀሳቀሳቸውን ምንጮች ገልጸዋል።