ሚያዝያ ፫ (ሦስት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ በሊቦ ከምከም ወረዳ አዲስ ዘመን ከተማ ላይ በወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ፣ ተጨማሪ ጥቃት ሊኖር ይችላል በሚል ቁጥራቸው ሁለት መቶ የሚሆኑ ወታደሮች ትናንት ምሽት ወደ ከተማዋ በመግባት በድሮው ፖሊስ ጣቢያና ፍርድ ቤት አካባቢዎች መስፈራቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል። ምሽቱን የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበር ነዋሪዎች ቢገልጹም፣ የተኩሱን መንስኤ ግን ለማወቅ አለመቻላቸውን ተናግረዋል።
በከተማ መስተዳደር ላይ ደርሶ ለነበረው ጥቃት አርበኞች ግንቦት7 ሃላፊነቱን መውሰዱ ይታወሳል።