መጋቢት ፳፮ (ሃያ ስድስት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህወሀትና የኢህአዴግ ከፍተኛ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ አባይ ጸሐየ ከመገናኛ ብዙሐን አመራር እና ከፖለቲካ ፓርቲ ተወካዩች ጋር በነበረው ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር “መገናኛ ብዙሐንፀረ ህዝብ እና የልማት እንቅፋት እንዲሆኑአኮላሽተናቸዋል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ይህ ችግር ከፓርቲዎች ጋር በሚደረግ ድርድርና ከግለሰቦች ጋር በመካከር አይሰተካከልም ያሉት የህወሃት አመራሩ አቶ አባይ ፤ “ብዙሐን መገናኛዎች እና ምክር ቤቶች ችግራችንን እንዳይነኩብን በማለት በተለያየ ጊዜአንራግረናል”ብለዋል።
“የኢህአዲኢግ ስራ አስፈጻሚ ህግ ሊያስከብር ይቅርና ራሱ የማያከብር ነው” በማለት አስፈጻሚውን አካል ክፉኛ የዘለፉት የህወሀቱ መሪ፤ “ አስፈፃሚው እዚህ ደረጃ ደረሰው ‘ሀይ’ የሚለው ያጣ ስለሆነ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።
እነኚህን ችግሮች ለማስተካከል በሚዲያ፣ በማህበራትና በምክር ቤት ደረጃ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ራሳቸው አጥንተው ጥሩ የተባለ መፍትሄ አቅርበዋል ያሉት አቶ አባይ ጸሀዬ “የቀረበውን የመፍትሄ ሀሳብ ተቀበል፣ አትቀበል የሚባለው ነገር ትግል ያስፈልገዋል። ዝም ብሎ አይቀበልም።በትግል ግን ይቀበላል”ብለዋል።