መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ ክልል በቡሌሆራ የተነሳውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ ጥቃት ይደርስብናል በሚል ተሸሽገው የቆዩ 12 ሰዎች ተይዘው መታሰራቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ሰዎቹ የተያዙት ከዚህ በሁዋላ ምንም እንደማይደርስባቸው በአገር ሽማግሌዎች ማረጋገጫ ከተሰጣቸው በሁዋላ ነው።
በአሁኑ ሰአት የአካባቢው ህዝብ በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኝ የገለጹት ምንጮች፣ በርካታ ሰዎች አካባቢውን ጥለው እየሸሹ ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ በቤንሻጉል ጉሙዝ ክልል በአሶሳ ከተማ ትናንት በርካታ ሱቆች መታሸጋቸው ታውቋል። ሱቆቹ የዋጋ ጭማሪ በማድረግና አድማ በማድረግ መታሸጋቸውን በእሽግ ወረቀቱ ላይ እንደሚታይ የአካባቢው ወኪል ዘግቧል።