መጋቢት ፳፩ (ሃያ አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ብዙ ኪሎሜትሮችን በእግር በመጓዝ ሕጻናትን የያዙ እናቶች፣ ነፍሰጡሮች እና አቅመ ደካማ ሶማሊያዊያን አገራቸውን እና መኖሪያ ቀያቸውን በመተው ኢትዮጵያ ውስጥ ወደሚገኘው ዳሎ አዶ መጠለያ ጣቢያ እየጎረፉ ነው።
ሶማሊያውያን በርሃብ የተጎዱ ልጆቻቸውን ማጥባት የተሳናቸው ሲሆን፣ አገራቸውን ጥለው ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱት ረሃብ እና ጦርነትን ሸሽተው መሆኑን ተናግረዋል።