ኢሳት (መጋቢት 12: 2009)
የቤኒሻንጉል ህዝብ ንቅናቄ (ቤህኒን) የሚካሄደው የነጻነት ትግል ሃገራዊና ከሌሎች ብሄሮች ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን የማዳን መሆኑን የድርጅቱ የፖለቲካ ሃላፊ ገለጹ።
የቤህኒን የፖለቲካ ሃላፊ አልሃጂ አፈንዲ ጠሓ በተለይ ለኢሳት እንደገለጹት በህወሃት/ኢሀዴግ የሚመራውን አገዛዝ ለማስወገድ የሚካሄደው የነጻነት ትግል ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ድርጁቱ በሃገር ውስጥ የሚካሄደው የትጥቅ ትግል በህወሃት/ኢህአዴግ ላይ ያነጣጠረ እንጂ በመሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት የማድረስ አላማ እንደሌለውም ገልጸዋል። በቅርቡ በህዳሴ ግድብ ላይ የተነጣጠረ ጥቃት ለማድረስ ተንቀሳቅሰዋል የተባለውንም ከቆምንለት አላማ ጋር የሚሄድ አይደለም ሲሉ አስተባብለዋል።