በቂልንጦ እስር ቤት ለወራት ክስ ሳይመሰረትባቸው የቆዩ እስረኞች የረሃብ አድማ ጀመሩ

መጋቢት ፲፪ (አሥራ ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምንጮች እንደገለጹት 19 ኢትዮጵያውያን ምንም አይነት ክስ ሳይመሰረትባቸው በእስር ቤት ውስጥ እየተሰቃዩ ነው። እስረኞቹ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ በተደጋጋሚ የእስር ቤቱን አመራር ቢጠይቁም፣ እስካሁን መልስ አላገኙም።
እስረኞቹ ከሰኞ ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት የሚቆይ የረሃብ አድማ በማድረግ ላይ ናቸው። እውቁ ፖለቲከኛ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ መሪ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ በርካታ እስረኞች በቂልጦ የረሃብ አድማ በማድረግ ላይ ናቸው።
የህሊና እስረኞቹ አድማውን የጀመሩት በእስር ቤት ውስጥ የሚታየውን የከፋ አያያዝ ለመቃወም ነው።