መጋቢት ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጋምቤላ ኒሎቴ አንድነት ንቅናቄ ለኢሳት በላከው መግለጫ በአሁኑ ወቅት ጋምቤላ ውስጥበታጠቁ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች እንዲሁም የንዌርና ሙርሌ ጎሳ በሆኑ የግመል አርቢዎች አማካይነት መጠነ ሰፊ ጥቃት እየተፈጸመ እነደሆነ በመጥቀስ ድርጊቱን አጥብቆአውግዟል።
እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር መጋቢት 1 ቀን 2017 አመተ ምህረት ከደቡብ ሱዳን የተነሱ የታጠቁየሙርሌ ሚሊሻዎች ድንበር አሳብረው በመግባት በኦቱዎል መንደር በጆር ቀበሌ ስምንት ሰዎችን ከገደሉና ሁለት ሰዎችን ካቆሰሉ በኋላ 16 ሕጻናትን አፍነው መውሰዳቸውንንቅናቄው ገልጿል።
በተመሣሳይ ወር በጆግና በዶር ቀጣናዎች በሚገኙ የተለያዩ ቦታዎች ተመሣሳይ ጥቃትና ጠለፋ መፈጸሙን የጠቀሰው ንናቄው ፤አሁን አሁን ይህ ድርጊት ጋምቤላ ባሉ ሲቪል አኝዋኮች ላይ የተለመደ ሆኗል ብሏል።ከአሁኑ ቀደም ብሎ በአጀሪንጋ እና በጂሎ አቦል መንደሮች በኑዌሮችና በሙርሌስ ታጣቂዎችበተፈጸመ ጥቃት ከ26 በላይ ሰዎች መገደላቸውንም የጋምቤላ ኒሎቴ አንድነት ድርጅት አውስቷል።
ከጥቃቱ የተረፉ ጥቂት ሰዎችም ቀያቸውን ጥለው እግራቸው ወዳመራቸው ቦታ መሰደዳቸው ተመልክቷል።
በሚገርም ሁኔታ በቅርቡ ማለትም ባለፈው የካቲት 27 ቀን በደቡብ ሱዳን አኝዋኮች ላይ በተፈጸመ ጥቃት ሦስት ሰዎች የመገደላቸውና ከአብዎቦና ከጎግ ቀጣናዎች ህጻናት መወሰዳቸውከፍተኛ ትኩረት አስነስቷል ያለው የንቅናቄው መግለጫ፤ ይህም በኢትዮጵያውያኑአኝዋኮች ላይ እየተፈጸመ ያለው መጠነ ሰፊ ጥቃት በህወኃት መንግስት ሆን ተብሎ የተቀነባበረ የዘርማጽዳትና ከመሬታቸው ላይ የማስወገድ ዘመቻ መሆኑን የሚያመላክት ነው ብሏል።
ይህ ኒሎቴዎች የገዛ ወንድሞቻቸውንና እህቶቻቸውን እየገደሉ ያሉበት ሂደት በትክክል በህወኃት መንግስት ስፖንሰርነት እየተፈጸመ ያለ የዘር ማጽዳት ዘመቻ መሆኑ ግልጽ ነው ሲልም ንቅናቄው በጉዳዩ ላይ ያለውን እምነት ገልጿል።
ህወኃት ይህን የሚያደርገውም የትግራይ ተወላጆችን በጋምቤላ ለማስፈር የጀመረውን አዲስእንቅስቃሴ ለማሳካት ነው ሲልም ድርጅቱ አስታውቋል።
ባለፈው ሳምንት ብቻ ከማዚ ዞን ሱርማ ቀጣና በርካታ የሱሪ ጎሳ አባላት መገደላቸውን፣ ብዙ ህጻናት ተጠልፈው መወሰዳቸውንና እጅግ በርካታ ከብቶች መነዳታቸውን የጠቀሰው ንቅናቄው፤ ይህ በግልጽ እየታወቀ በመንግስት የተወሰደ ምንም አይነት እርምጃ አለመኖሩንአመልክቷል።
በአሁኑ ጊዜ በጋምቤላ እየተፈጸመ ያለው ጥቃት፣ በህወኃት -ኢህአዴግ መንግስት እና በትዋት ፓል በሚመራው ከንዌር ጎሳ በሆነው የቀድሞ ተቃዋሚ ድርጅት መካከል ከመጋረጃ ጀርባ በተደረገ ስምምነት ነው ብሎ እንደሚያምን ንቅናቄው ገልጿል።
ቀደም ሲል ተቃዋሚ የነበሩት ትዋት ፓል የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎችን ትግል በመክዳት ባለፈው ዓመት ለህወኃት መንግስት መግባታቸው ይታወቃል።በአጠቃላይ በክልሉ እየተፈጸመ ያለው ጥቃት የህወኃት የበላይነት የሚንጸባረቅበት መንግስትጨካኝ፣ ፋሽስት፣አምባገነንና ቅን ገዥ መሆኑን የሚያመላክት ነው ያለው ንቅናቄው፤ ያለኢትዮጵያ ሕዝብ ይሁኝታ በስህተት ስልጣን ላይ ይገኛል ያለውን ሥርዓት ለመቀዬትሰፊና ፈጣን ሕዝባዊ ምላሽ እንደሚያስፈልግ አስምሮበታል።የኒሎቲክ ጎሳ አባላትም በገዛ ወንድምና እህቶቻቸው ላይ እንዲነሱ ሆነ ተብሎ የተቀነባበረውንሴራ እንዲያወግዙ ንቅናቄው ጥሪ አቅርቧል።
የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት፣ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር፣ የሰብአዊ እርዳት ድርጅቶች እና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ዓለማቀፍ ድርጅቶች ሁሉ ወደ ስፍራው በመንቀሳቀስ በተለይ በደቡብ ሱዳን-ጎሮን ባሉ የጋምቤላ ስደተኞች ላይ ያለውን የደህንነት ስጋት እንዲመለከቱና ስደተኞቹ ወደተሻለ ቦታ እንዲሰፍሩ ያደርጉ ዘንድ ጥሪ አቅርቧል።
እንዲሁም የህወኃት መንግስት በኢትዮጵያውያኑ ኒሎቴዎች ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያ እንዲያቆምና በተለያዩ ወህኒ ቤቶች አስሮ እያሰቃያቸው ያሉትን የኒሎቴ ጎሳ አባላት እንዲፈታ የጠየቀው ንቅናቄው፤ በመንግስታቱ ድርጅት ህግጋት መሰረት ወደ ገዛ መሬትባለቤትነቸው እንዲመለሱ፣ የይዞታ ክልላቸው እንዲከበር፣ገለልተኛ የልማት እንቅስቃሴያቸውና የውጪ ፖሊሲያቸው እንዲረጋገጥ ጥሪ አቅርቧል።
መግለጫው በመጨረሻም የንቅናቄው ሰራዊት የጋምቤላ ህዝብንና የደቡብ ም ዕራብ ኒሎቴዎችን ነጻነት፣ ደህንነት፣ ፍትህና ክብር ለማረጋገጥ የጀመረውን ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።