የኢህአዴግ ምክር ቤት የሁለት ቀናት ውይይት በሃሰት ሪፖረት ተጠቀቀ፡፡

የካቲት ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ ፣ ህዝቡ በአስቸኳይ አዋጁ ስለተረጋጋ ‹‹እየታደሰን እንሰራለን ፤ እየሰራን እንታደሳለን›› የሚል መርህ ይዞ እንደሚቀጥል ገለጸ።የድርጅቱ ምክር ቤት ባወጣው ሪፖርት፣ ተሃድሶው ስኬታማ ነው ቢልም ማዕከላዊ ኮሚቴው ባቀረበው ሃሳብ መሰረት የአስቸኳይ አዋጁ እንደማይነሳ በውይይቱ መግባበት ላይ ደርሷል፡፡
ኢሃዴግ እንደ ጤነኛ ደርጅት እራሱን እያወደሰ በተነጋገረበት በዚህ መድረክ፣ እኛ ለፖለቲካውትኩረት በሰጠነው ቁጥር የበለጠ ፖለቲካዊ ኪሳራ እየገባን ስለሆነ አሁን ከፍተኛ ስጋት ወደ ደቀነብን ወቅታዊ ድርቅ ብናተኮር የተሻለ ነው ብሏል።
በኦሮምያ እና ሶማሌ ክልል የተነሳውን የእከክ እና የኮሬላ ወረርሽኝ ጊዚያዊ የሃኪሞች ቡድን ለመቆጣጠር እንዳልቻለ አና በአካባቢው በተቀሰቀሰው ረሀብ ምክንያት በመቶዎች የሚቆጥሩ ሰዎች መሞታቸውን ያወሳው ምክርቤቱ ፤ አዲስ የተሾሙ ሚንስትሮቸ ምክር ቤቱን ይቀላቀሉ አይቀላቀሉ በሚለው ዙሪያተወያይቶ፣ የማቀላቀሉን አስፈላጊነት በሌላ ጊዜ መረጃ ይዞ ለመነጋገር ወስኖ ተለያይቷል፡፡
“የተሃድሶው ንቅናቄ አበረታች ውጤት ነው፤ በሀገራችን የሚታየውን ችግር እየፈጠሩት ያሉት ጠባብተኛነት እና ትምክህተኛነት ናቸው እነሱን እንታገላለን”ያለው ገዥው ፓርቲ፤ “ህዝቡን የምንይዝበንት አጀንዳ በተከታታይ መቅረፅ ላይ ማተኮር የተሸለ ነው” ብሎአል፡፡
ከኦሮምያ በስተቀር በመላ ሀገሪቱ በተካሄደው የህዳሴው ግድብ ሩጫ ላይ የአመፅ ምልክት አለመታየቱ የተሃድሶው አንዱ ውጤት መሆኑን ኮሚቴው በቃለ ጉባኤ ላይ አሰፍሯል፡፡”ረሃቡ ፈተኝ ነው” ያለው የኢሀአዴግ ስራ አስፈፃሚ” ይህ በሆነበት ሁኔታ የውጭ ምላሽ አንሰተኛ ነው ብሏል።