በአማራ ከልል የተለያዩ ወረዳዎች መምህራን የስራ ማቆም አድማ ጀመሩ

የካቲት ፳፰ ( ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከተለያዩ ወረዳዎች የደረሱን መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በምእራብ ጎጃም ዞን በአዴት፣ በሰቀላ ደግሞ መምህራን አድማ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርጉ የተወሰኑ መምህራን ታስረዋለ። በምሰራቅ ጎጃም ደብረወርቅ ፣ ሸበል በረንታ ፣ ቡብኝ፣ በቻግኒ እንዲሁም በድቡብ ጎንደር ደራ ወረዳ የአፈር ዋናት ሁለተኛ ደረጃ መምሀራን የስራ ማቆም አድማው መንሳኤ ለሌሎች የመንግስት ሰራተኞቸ የደሞዝ ጭማሪ ሲደረግ፣ ለመምሀራን ተዘሏል የሚል ነው። በአዲስ አበባ ለመምህራን መኖሪያ ቤት እንስጣለን በሚል፣ መምህሩ በአደማው እንዳይሳተፍ ለማግባባት ሲሞከር ሰንብቷል።
የኑሮ ውድነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨምር ለመምህራን ፈተና ሆኗል።