የካቲት ፳፰ ( ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ቀጨኔ ልዩ ስሙ ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ ህዳሴ በሚባል ጤና ጣቢያ ውስጥ ነርሶች ለወላዷ የምጥ መርፌ ከወጉዋት በሁዋላ ፣ ከወላዱዋ ርቀው ሲጫውቱ ቆይተው ሲመለሱ ህይውቱዋ አልፎ ያገኙዋት ሲሆን፣ በዚህ ድርጊት የተብሳጩት የአካባቢው ነዋሪዎቸ የጤና ጣቢያውን በሮችና መሰኮቶች በድንጋይ ሰባብረዋል። ወላዱዋ ከቀኑ 8 ሰአት ላይ እንደገባችና ምሽት ላይ መርፌው እንደተስጣት ታውቋል።
የወላዷ የቀብር ስነስራትም ሰኞ በቀጨኔ መድሃኒያለም ተፈጥሟል።