የካቲት ፳፬ ( ሃያ አራት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከጎንደር ብአዴን ጽ/ቤት በተገኝው መረጃ መሰረት በጎንደር ከተማ የተነሳውን ተቃውሞ ለማብረድ እና ሴቶችን ያማካለ ሰላም የማምጣት ስትራቴጅ በሚል በታቀደው መሰረት ከመንግስት በጀትና በG.F በጎንደር ከተማ በግሎባል ፈንድ ከተለገሰው ገንዘብ ተቀንሶ በብአዴን ስም የተለገሰ እና በረጅም ጊዜ ተመላሽ የሚሆን ከወለድ ነፃ የገንዘብ ድጋፍ ስራ በ1ኛ ዙር ለተመረጡ 657 ሴቶች ለእያንዳንዳቸው 8 ሺ 790 ብር በዳረንጎት መልክ ተሰጧል፡፡
ለአመጽ ተጋላጭ ሴቶች ተብለው ለተለዩት የጎንደር ከተማ ሴቶች የተሰጠው ገንዘብ የከተማውን ህዝብ ተቃውሞ የሚያበርደው እንደማይሆን የአብዴን የጎንደር ከተማ አባላት ይናገራሉ።