የአባይ ድልድይ በመዘጋቱ ከፍተኛ ችግር ተፈጥሯል

ጥር ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዓፄ ኃይለሥላሴ ዘመን የተገነባው የጎጃም ጎንደር አባይ ድልድይ ከዛሬ ጠዋት 4:00 ሰዓት ጀምሮ በቆርቆሮ ተዘግቶ አገልገሎት መስጠት አቁሟል ፡፡
ከጎንደር እና ከጎጃም የሚመጡ መሻገር የግድ የሆነባቸው ተሽከርካሪዎች በሶስት ረድፍ ተሰልፈው በአማራ ልዩ ኃይል ፈቃድ አልፎ አልፎ በድልድዩ አንድ መስመር ብቻ ተሽከርካሪዎች እንዲያልፉ እየተደረገ ሲሆን፣ ህዝቡ በከፍተኛ ምሬት በእግሩ እየተጓዘ ነው።
በእድሜ የገፉ ሰዎች “ ከምን አይነቱ ጊዜ ደረስን” በማለት ምሬታቸውን ሲገልጹ መሰማታቸውን ወኪላችን ገልጿል። ድልድዩ የመፍረስ አደጋ ተደቅኖበት እንደነበር ኢሳት ከወራት በፊት መዘገቡ ይታወሳል።