ጥር ፳፮ (ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በክልሉ 55 ሆስፒታሎች ቢኖሩም የቀዶ ህክምና የሚሰጡት ሰባቱ ሪፈራል ሆስፒታሎች ብቻ ናቸው።እነዚህም በአግባቡ መስጠት የሚያስችል አቅም የላቸውም::ሆስፒታሎች በጣም አነስተኛ ከመሆናቸው ጋር ታካሚዎች ህክምናውን ለማግኘት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ለተለያዩ ወጪዎች ይጋለጣሉ።
ሁሉም ሆስፒታሎች ከፍተኛ የባለሙያ እና የቁሳቁስ እጥረት አጋጥሟቸዋል። ገዢው ፓርቲ በጤናው መስክ የሚሊኒየሙን የልማት እቅድ አሳክቻለሁ ቢልም፣በአገሪቱ በሚገኙ የጤና ተቋማት ከፍተኛ የሆነ የባለሙያና የቁሳቁስ እጥረት ይታያል።