ህዳር 22 ቀን 2004 ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የመለስ መንግስት የስልክና የኢሜል መልእክቶችን ለመጥለፍ እንዲሁም የሳተላይት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ለማፈን የሚጠቅመውን ቴክኖሎጂ ከህንድና ከቻይና ኩባንያዎች መግዛቱን ዊኪሊክስ አጋለጠ
ዊኪሊክስ በዋጣው አዲስ መረጃ በአለም ላይ ለዚሁ ተግባር የቴክኖሎጂ ውጤቶችን የሚሸጡ የ150 ኩብንያዎችን ስም ይፋ አድርጓል።
የዊኪሊክሱ መስራችን ባለቤት የሆነው ዊሊያም አሳንጄ ለዘ ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ እንደተናገረው አንድ የህንድ ኩባንያ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ የስለላና የማፈኛ መሳሪያዎችን ለኢትዮጵያ መንግስት መሸጡን ከኩባንያው ፋይል አንብቤአለሁ” በማለት አጋልጠዋል።
ሀይማካል ፕራዴሽ የተባለው የህንድ ኩባንያ የሳተላይት መስመሮችን፣ ከኢንል ሳት፣ ኢዩቴል ሳት፣ አረብ ሳት፣ ቱርክሳት የሚተላለፉ የሲና የኬዩ የቴሌቬዥንና የራዲዮ የሳተላይት ስርጭቶችን እንደሚያፍን ዘ ሂንዱ የተባለው የህንድ ጋዜጣ ዘግቧል።
በዊኪሊክስ መረጃ መሰረት የማፈኛና የስለላ ቴክኖሎጂዎችን ለአምባገነን መንግስትታ ከሚሸጡት የህንድ ኩባንያዎች መካከል ሾጊ ኪሚኒኬሽን፣ ክሊር ትሬል፣ ሺልድ ሴኩሪቲ የሚገኙበት ሲሆን፣ የቻይናዎቹ ዜድ ቲኢ፣ ሀዋይ ቴክኖሎጂና ቪክስቴልም ተጠቅሰዋል።
13 ሚሊዮን ህዝብ በእርዳታ በሚኖርባት ኢትዮጵያ ፣ መንግስት በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በማፍሰስ የህዝብን ስልክና የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ለመጥለፍ እንዲሁም ሰተላይት ሬዲዮኖችንና ቴሌቪዥንኖችን ለማፈን ሙከራ እንደሚያደርግ በተደጋጋሚ ተዘግቧል።
ዊሊያም አሳንጄ አምባገነን መንግስታት ስልጣናቸውን ለማቆዬት ሲሉ በብዙ ቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በማፍሰስ እነዚህን የረቀቁ ቴክኖሎጂዎች እንደሚገዙ በድረገጹ ላይ አስፍሯል።