ገዢው ፓርቲ የአቶ ዲንቃ ደያሳን ንብረት አገደ

ታኅሣሥ ፳፬ (ሃያ አራት)ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- በኦሮሞያ የሚካሄደውን ተቃውሞ ይደግፋሉ እንዲሁም  ለአባገዳዎች ግብዣ አድርገዋል የተባሉትና በአሁኑ ሰአት ውጭ በስደት የሚገኙት አቶ ዲንቃ ደያሳ፣ ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ኮሌጃቸው ጨምሮ ሶደሬ አካባቢ የሚገኘው መዝናኛ ክበባቸው  እንዲታገዱባቸው ተደርጓል።

ሰደሬ አካባቢ ያለው መዝነኛ 76 ሚሊዮን ብር የታክስ እዳ አለበት በሚል ሰበብ እንዲዘጋ መደረጉንም ምንጮች ገልጸዋል። ሪፍት ቫሊ  የዛሬ 17 አመት በ1.3 ሚሊዮን ብር ካፒታል በአምስት ባለሃብቶች የተቋቋመ ነበር።

በኦሮምያ ከተካሄደው ህዝባዊ ንቅናቄ ጋር በተያያዘ በርካታ ባለሃብቶች ማእከላዊ ታስረው ይገኛሉ።