ታኅሣሥ ፳፬ (ሃያ አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባ መስተዳደር በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ በወረዳ 9፣ 10፣ 11፣ 12 እና 13 የሚገኙ ቤቶችን ለማፍረስ ማስታወቂያ ካወጣ በሁዋላ፣ በወረዳ 10 እሁድ ህዝቡ ለስብሰባ የተጠራ ሲሆን፣ በከፍተኛ የቁጣ ስሜት ውስጥ የነበረው ህዝብ “ እኛ የእናንተን ውሸት መስማት ሰልችቶናል፣ በቃችሁን፣ ቤታችንን አታፈርሱትም፣ ደጃፋችን ላይ እንሞታለን፣ ሂዱልን” በማለት ስብሰባው እንዲበተን ተደርጓል።
ህዝቡም መስተዳድሩ እንዲህ አይነት እርምጃ ከመውሰዱ በፊት ቆም ብሎ እንዲያስብ አሰጥንቅቋል።