ታኅሣሥ ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዳንሻ ይኖሩ የነበሩት የወልቃይት የአማራ ማንነት የኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ግዛው በሬ ተደጋጋሚ ማስፈራሪያና ዛቻ ሲፈጸምባቸው ከቆዩ በሁዋላ ትናንት ማክሰኞ ሶረቃ ከተማ በስራ ላይ እያሉ በትግራይ ክልል የደህንነት አባላት ታፍነው ተወስደዋል።
አቶ ግዛው በዳንሻ መኖር ስላልቻሉ ወደ ሰሮቃ ሄደው በግል ስራ ላይ ይተዳደሩ ነበር። ግለሰቡ እስካሁን ድረስ የት ቦታ እንደታሰሩ የታወቀ ነገር የለም።
በሌላ በኩል የታህሳስ ባአታ በአል በሚከበርበት ወቅት አርማ የሌለውን የኢትዮጵያ ሰንደቅላማ በቤተክርስቲያኑ ዙሪያ እንዲሰቀል አድረገዋል የተባሉት እና ለሳምንታት የጠፉት አባ ቀለምወርቅ መታሰራቸውን ምንጮች ገልጸዋል።