በአፋር ክልል የተተከለው ራዳር መነሳቱ ታወቀ

ታኅሣሥ ፲፯ (አሥራ ሠባት)ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- በቅርቡ በተለያዩ አገሪቱ ክፍሎች ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ወጥቶባቸው ከተተከሉት ራዳሮች መካከል በአፋር ክልል ዱብቲ አካባቢ የተተከለው ራዳር ሳምንት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ እንዲነቀል ተደርጓል። እርምጃው ለምን እንደተወሰደ ባይታወቅም፣ ዘገባው በኢሳት ከተላለፈ በሁዋላ እንዲነሳ መደረጉ ምናልባትም ከመረጃው ከመውጣት ጋር የተያያዘ ሳይሆን እንደማይቀር ይገመታል።

ከፍተኛ ገንዘብ ወጪ በማድረግ ገዢው ፓርቲ የተለያዩ የርቀት መቆጣጠሪያ መሳሪያዎችን እንዲሁም የጦር መሳሪያዎችን እያስገባ መሆኑን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

በርካታ የሩሲያ መኮንኖች ወደ አገሪቱ ገብተው ምክር በመስጠት ላይ ሲሆኑ፣ የመሳሪያ ተከላዎችም በእነዚህ መኮንኖች ክትትል የሚካሄድ መሆኑን መረጃዎች የመለክታሉ።