ቤተ እስራኤላዊያን የሚደርስባቸውን ዘረኝነት በመቃወም ብሄራዊ ወታደራዊ አገልግሎትን ተቃወሙ

ታኅሣሥ ፲፯ (አሥራ ሠባት)ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- ቁጥራቸው 300 የሚሆኑ ቤተእስራኤላዊያን በተቋም ደረጃ በእስራኤል ውስጥ የሚደርስባቸውን ዘረኝነትና መገለል በመቃወም ወታደራዊ አገልግሎት ለመስጠት ፍቃደኛ አይደለንም ሲሉ ተቃውሞ አደርገዋል። ቤተእስራኤላውያኑ በእስራኤል መንግስት መስሪያቤቶች በወታደራዊ እና ፖሊስ ተቋማት ውስጥ መገለል እንደሚደርስባቸው ተናግረዋል።

እነዚህ 300 ኢትዮእስራኤላዊ አይሁዶች በወታደራዊ አገልግሎት በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች ላይ ያገለግሉ የነበሩ ናቸው።