የአምቦ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንደተዘጋ ነው

ታኅሣሥ ፲፬ (አሥራ አራት)ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- ከሁለት ቀናት በፊት  የአምቦ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ያነሱትን ተቃውሞ ተከትሎ፣ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ላለመሄድ በመወሰናቸው ዛሬ አርብ፣ ትምህርት ቤቱ ተዘግቶ ውሎአል። ባለፈው ረቡዕ በተደረገው ተቃውሞ ሳቢያ በርካታ ተማሪዎች ከፍተኛ ደብደባ የተፈጸመባቸው ሲሆን፣ ተማሪዎቹ ዛሬ ትምህርት ይጀምራሉ ተብሎ ቢጠበቅም ሳይሳካ ቀርቷል።

ከአምቦ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውጭ ያሉ ሌሎች ትምህርት ቤቶችም ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው የፌደራል ፖሊሶች እየተጠበቁ ነው። የታሰሩት ተማሪዎች አሁንም አለመለቀቃቸው ታውቋል።

በሌላ በኩል ረቡዕ እና ሃሙስ ከአርሲ የታፈሱ ወጣቶችና ጎልማሶች በሌሊት ተጭነው ሰንቀሌ ወታደራዊ ካምፕ መግባታቸውን ምንጮች ገልጸዋል። በአንድ በኩል 10 ሺ ሰዎች እንደተፈቱ በመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ቢነገርም፣ በሌላ በኩል ግን አሁንም በርካታ ወጣቶች እየታፈሱ ወደ እስር ቤት እየተጋዙ ነው።