አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ህገመንግስታዊ ማሻሻያ ለማድረግ የመነሻ ሃሳብ እንዲቀርብላቸው ጠየቁ

ታኅሣሥ ፲፬ (አሥራ አራት)ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- በአገሪቱ ውስጥ የተፈጠረው ህዝባዊ ንቅናቄ ስርዓቱን አደጋ ውስጥ መጣሉን የተረዳው ኢህአዴግ፣ መነጠኛ የህገ መንግስት ማሻሻያ ለማድረግ የሚያስችል ጥናት እንዲቀርብለት በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በኩል ትእዛዝ አስተላልፏል። ጥናቱ በሁለት ወራት ውስጥ ተጠናቆ እንዲቀርብ ያዛል። ክልሎቹን ህገመንግስቱን ለማሻሻል የሚያስችል አቅም ያላቸው አፈ ጉባኤ ጽ/ቤት አመራሮች ምርጫ አካሂደው እንዲያሳውቁ ታዘዋል።

የሚሻሻሉት ህጎች የትኞቹ እንደሆኑ ባይታወቅም፣ ምናልባትም ከክልሎች ስልጣን ጋር በተያያዘ መጠነኛ ለውጦች ሊኖሩ እንደሚችሉ ይገመታል።