ታኅሣሥ ፲፩ (አሥራ አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ግንባሩ፣ ባለፈው ሃሙስ በኦጋዴን ቃብሪዳህር ወረዳ ዲሞዲሊ መንደር ውስጥ የህወሃት ኢህአዴግ ታጣቂዎች በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ እንደተለመደው የጅምላ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈርና እስራት መፈጸማቸውን ተከትሎ ግንባሩ ከተጠቂዎቹ ጎን በመቆም አጸፋዊ ምላሽ መውሰዱን አስታውቋል።
በሁለቱ ቡድኖች መሃከል በተደረገው የተኩስ ልውውጥ 6 የህወሃት ኢህአዴግ ወታደሮች ተገለው፣ 8 መቁሰላቸውን የግንባሩ ወታደራዊ ክንፍ አስታውቋል። በኦጋዴን ግዛት ውስጥ የገዥው ፓርቲ ወታደሮች እና የክልሉ ልዩ ጦር በቀጠናው በተደጋጋሚ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በከፋ ሁኔታ መፈፀም መቀጠላቸውን ግንባሩ በላከው መግለጫ አብራርቷል።