ማላዊ 100 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ወደ ትውልድ አገራቸው መለሰች

ታኅሣሥ ፯ (ሰባት)ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- ማላዊን አቆራርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ በሕገ ወጥ መንገድ ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ቁጥራቸው 100 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ከዓለምአቀፉ የደተኞች ድርጅት(IOM) ጋር በመተባበር ወደ ትውልድ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉን የማላዊ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር ቤስተን ችላቢሊ አስታወቁ።

ሚንስትሩ ቀደም ብሎ 300 ኢትዮጵያዊና ስደተኞች ከማላዊ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ መደረጋቸውን ገልጸዋል። በማሉፓ እስር ቤት ውስጥ150 ስደተኞች መኖራቸውን ኒያሳ ታይምስ ዘግቧል።