ኅዳር ፳ (ሃያ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜናዊ ምዕራብ ኬንያ በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ነዋሪ የሆኑ ዜጎች ቁጥራቸው ከ10 ሽህ በላይ የሚሆኑ ቤተሰቦች መኖሪያ ቀያቸውን በመተው ወደ ኡጋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኢትዮጵያ ተሰደዱ። የአካባቢው ነዋሪዎችን ለስደት ያበቃቸው ለከብቶቻቸው የግጦሽ ፣ ለምግብ እና የመጠጥ ውሃ ፍለጋ ሲሆን በድርቁ ምክንያት ከአንድ ሺህ በላይ የቤት እንስሳት ሞተዋል።
ተፈናቃዮቹ በኡዳንዳ ከፍተኛ ተግዳሮቶች እንደተደቀኑባቸው ሲቲዝን ዘግቧል። የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ቱርካና ሃይቅ የሚገቡ ተፋሰሶሶችን በመዝጋት ለስኳር ፕሮጀክት መጠቀም ከጀመረ ውዲህ በኢትዮጵያ እና በኬኒያ የሚኖሩ አርብቶ አደሮች ላይ ከፍተኛ አደጋ መጋረጡ ይታወሳል።