በፍኖተሰላም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች ሰፈሩ

ኅዳር ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :-የከተማዋ ነዋሪዎች እንደገለጹት በደንብ የታጠቁ ወታደሮች ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ወደ ከተማው የገቡ ሲሆን፣ የጃቢ ጠናን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጽ/ቤት ግቢን ካምፕ አድርገውታል።

በከተማው በብዛት የሚታዩት ወታደሮች ናቸው የሚሉት ነዋሪዎች፣ እነሱ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ በከተማው ውጥረት መጨመሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ወላጆችን “ልጆቻችሁን በጊዜ ወደ ቤታችሁ አስገቡ” እያሉ መሆኑን የተናገሩት ነዋሪዎች፣ ህዝቡ መታወቂያ እንዲያሳይ ሲጠየቅ፣ ለመተባበር ፈቃደኛ አልሆነም ይላሉ።

በፍኖተሰላም አካባቢ የሚኖሩ ወታደሮች ራሳቸውን በማደራጀት የነጻነት ትግል በማድረግ ላይ ናቸው። በቅርቡ በብርሸለቆ መንገድ ላይ በፈጸሙት ጥቃት በርካታ የመንግስት ወታደሮች መገደላቸውን ኢሳት ዘግቦ ነበር።