በዳባት ወረዳ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ታጋዮች ከህወሃት ወታደርጎች ጋር ከፍተኛ ውጊያ ማካሄዳቸው ተገለጸ

ኢሳት (ኅዳር 17 ፥ 2009)

በዳባት ወረዳ በጃኖራ ቀበሌ ልዩ ስሙ መንደርጌ ተብሎ በሚጠራ ቦታ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ታጋዮች ከህወህት ወታደሮች ጋር ከፍተኛ ወጊያ በትናንትናው ዕለት እንዳካሄዱ የአካባቢው ምንጮች ለኢሳት ገለጹ።

ህወሀት በውጊያው ያሰለፋቸው ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት በመድረሱ አጋዥ ሀይል ለማስገባት እንቅስቃሴ ላይ ማደርጉ ታውቋል።

ህወሃት በጭላ ማርያም እና በበንከር ልደታ በኩል ተጨማሪ ወታሮችን ለማስገባት የሞከረ ሲሆን አብዛኛው ህብረተሰብ ይህንን በማወቅ ከነጻንት ሀይሎች ጋር ተቀላቅሎ እገዛ ማድረጉ ታውቋል።

የኢሳት ምንጮች እንዳስረዱት ህወሀት መራሹ መንግስት ተጨማሪ ጦር ወደ አካባቢው እያዘመተ በመሆኑ የአምባ ጊዮርጊስ፥ የገደብዬ እና የዳባት ህዝብ በነቂስ በመወጣት መንገድ በመዘጋት ድጋፍ እንዲያደርገም ጥሪ ቀርቧል።

አርብ በተደረገ ውጊያ ወደ 50 የሚጠጉ ወታደሮች መሞታችው የታወቀ ሲሆን ስደስት ያህል የቆሰሉና የተማረኩም እንዳሉም የአይን እማኞች ከስፍራው አስረድተዋል።

በሌላ በኩል የገዢው ስርዓት ህወሀት መንግስት ማርኬአቸዋልሁ እያለ የሚናገርው ሰዎች በዳንሻ ከሚገኝ  ርህሳ ከሚባል ሰፈራ ጣቢያ ከትግራይ ክልል መጥተው የሰፈሩ መሆናቸውን ምንጮቻችን ጠቅሰዋል።

በተለያዩ አቅጣጫዎች የተነሱብትን ሕዝባዊ ትግሎች ለማሳነስ ሕብረተሰቡን የሚያደናግር ከፍተኛ ሰራ እየሰራ መሆኑን ምንጮቻችን ጨምረው አስረድተዋል።