ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ለህገወጥ የሰዎች ዝውውር አደጋ በመጋለጥ ላይ  ናቸው ተባለ

ኢሳት (ኅዳር 15 ፥ 2009)

የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት መቀዝቀዝ ማሳየቱን ተከትሎ በርካታ የሃገሪቱ ሴቶች ለህገወጥ የሰዎች ዝውውር አደጋ በመጋለጥ ላይ መሆናቸውን ሮይተርስ የተለያዩ አካላትን ዋቢ በማድረግ ሃሙስ ዘግበ።

በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ችግር ዙሪያ ጥናትን የሚያካሄደው ዎክ ፍሪ የተሰኘ ተቋም በበኩሉ ከ400ሺ የሚበልጡ ኢትዮጵያውያን የባርነት አይነት ህይወት ውስጥ እንደሚገኙ በ2016 ረፖርቱ አስፍሯል።

በኢትዮጵያ የሚኖሩ አብዛኞቹ ሴቶች በረሃብ፣ በህመም፣ በድህነትና ተያያዥ በሆኑ ችግሮች ዙሪያ ህይወታቸውን እየመሩ መሆኑን በሴቶች መብት መከበር ዙሪያ የሚሰሩ አካላት ለዜና አውታሩ አስረድተዋል።

At least 8.2 million Ethiopians are in need of food aid, the government says, as the country braces for the effects of the El Niño weather phenomenon. An inter-agency assessment, led by the government, conducted in September 2015, identified 3.6 million people in need of food assistance â in addition to 4.55 million from the previous month. Plan International Ethiopia is responding to the food security crisis and has identified 5,387 sponsored children who have been affected. We are currently working with at-risk communities to prioritise the needs of children by implementing emergency nutrition response and livelihood recovery programmes in three of the most affected districts with funding support from USAID/OFDA.

አብዛኛውን የሃገሪቱን የህብረተሰብ ክፍል የሚወክሉት እነዚሁ ሴቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያለባቸው ችግር ከመቅረፍ ይልቅ ተጨማሪ ችግሮች እየደረሱባቸውና በህገወጥ የሰዎች ዝውውር መዳረጋቸውን የሴቶች መብት ተሟጋች የሆኑት ወ/ሮ ቦጋለች ገብሬ ለሮይተርስ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መቀዛቀስ ማሳየት በመጀመሩ ሳቢያ የሴቶቹ ችግር እየተባባሰ መምጣቱን የዜና አውታሩ አመልክቶ ሃገሪቱ ካሉት 99 ሚሊዮን ህዝብ መካከል ሁለት ሶስተኛ የሚሆነው ገቢው ከሁለት ዶላር በታች መሆኑን ዘግቧል።

የመንግስት ባለስልጣናት በተያዘው አመት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ12 በመቶ ያድጋል ቢሉም የአለም ባንክ እድገቱን በግማሽ በማሳነስ ኢኮኖሚያዊ እድገቱ በስድስት በመቶ አካባቢ ብቻ ሊያድግ እንደሚችል ትንበያው አስቀምጧል።

ባንኩን ጨምሮ የተለያዩ አለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት የኢትዮጵያ ውጭ ንግድ ካለፉት ጥቂት አመታት ወዲህ ከፍተኛ ቅነሳ በማሳየቱ ምክንያት የሃገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት መዋዠቅ በማሳየት ላይ መሆኑን ይገልጻል።

ይኸው ኢኮኖሚያዊ አለመረጋጋት በተለይ በሴቶች ህይወት ላይ ጉዳትን በማስከተል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴቶች ህይወት አደጋ ውስጥ መውደቁ ተመልክቷል።

ዎክ ፍሪ የተሰኘ ተቋም በበኩሉ ከ400 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን የባርነት አይነት ህይወት ውስጥ እንደሚኖሩ በተያዘው አመት ባወጣው ጥናታዊ ምርምር ይፋ አድርጓል።

በተያዘው የፈረንጆች አመት ተመሳሳይ ሪፖርትን በዚሁ ጉዳይ ዙሪያ አውጥቶ የነበረው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ ዕድሚያቸው ስምነት አመት የሆናቸው ህጻናት ሳይቀሩ አዲስ አበባ ውስጥ በሴተኛ አዳሪነት ተሰማርተው እንደሚገኙ ገልጿል።

በቅርቡ በዚሁ በአሜሪካ በሚካሄድ የሴቶችና የህገወጥ ሰዎች አለም አቀፍ ጉባዔ ላይ የኢትዮጵያ ሴቶች ችግር መወያያ ሆኖ እንደሚቀርብ ለመረዳት ተችሏል።