ኅዳር ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ቀውስ አጥኚ ቡድን ከ ኢትዮጵያ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን ጋር በመተባበር የድርቅ አደጋ ያንዣበባቸውን አካባቢዎች ለይተው አውጥተዋል። በደቡባዊ ምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢ አርብቶ አደሮች ለረሃብ አደጋ ተጋላጭ ሆነዋል። ለጉዳተኞቹ እርዳታዎችን ለማሰራጨት አስቸኳይ አዋጁን ተከትሎ የፀጥታ ችግሮች መኖራቸው እና መንገዶች ዝግ መደረጋቸው የሰዎችን ሕይወት ለመታደክ ከፍተኛ ሳንካ ፈጥሯል።
በአፋር ክልል ዱብቲ፣ ኤሊዳር እና ሰርዶ ወረዳዎች፣ ሶማሊያ ክልል ዶሎ አዶ ዞን እና በ236 የክልሉ ወረዳዎች እና በኦሮሚያ ክልል በባሌ፣ ጉጂ፣ቦረና ዞኖች ነዋሪ የሆኑ አርብቶ አደሮች በውሃ እጥረት ምክንያት እንስሶቻቸው እየሞቱ የአርብቶ አደሮቹን ሕይወት ሰቆቃ ማድረጉን አጥኚዎቹ አስታውቀዋል። ከኢሬቻ እልቂት በኋላ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክልሎች እንደልብ መዘዋወር አስቸጋሪ እየሆነ ከመምጣቱም በተጨማሪ የምግብ እጥረት ከኢሬቻ እልቂት በኋላ በአብዛሃኛው የኢትዮጵያ ክልሎች እንደልብ መዘዋወር አስቸጋሪ እየሆነ ከመምጣቱም በተጨማሪ የምግብ እጥረት ያለባቸውን አካባቢዎች የረድኤት ድርጅቶች እርዳታ ለማቅረብ የጸጥታ ችግሮች ተፈጥሯል። በምእራብ አርሲ ዞን የእህል መጋዞኖችን ጨምሮ የእርዳታ እህል የጫኑ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት ደርሶባቸዋል። ይህም የእርዳታ ስርጭቱ ላይ ከፍተኛ ተግዳሮት አስከትሏል።
አስቸኳይ አዋጁን ተከትሎ መንገዶች ዝግ መሆናቸውን የፀጥታ አለመረጋጋት መፈጠሩ በኢትዮጵያ ከተከሰተው የድርቅ አደጋ ጋር ተደምሮ ከፍተኛ እልቂት ሊፈጠር ይችላል የሚል ስጋት መኖሩን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ቀውስ አጥኚ ቡድን ማሳሰቡን ሪሊፍ ዌብ ዘግቧል።