ኅዳር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመረጃ ኔትወርክ እንዳስታወቀው በኦሮምያ በተለይም በቦረና አካባቢ፣ በደቡብና ሶማሊ አካባቢዎች ከፍተኛ የሆነ የምግብና የውሃ እጥረት ተከስቷል። አርብቶአደሮች እንስሶቻቸውን ይዘው ምግብ እና ውሃ ፍለጋ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን የገለጸው ድርጅቱ፣ አፋጣኝ አለማቀፍ እርዳታ ካልተገኘ ድርቁ የከፋ ጉዳት ያስከትላል ብሎአል።
የአለማቀፉ የምግብ ድርጅት ለአስቸኳይ እርዳታ በሚል 14 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ጠይቋል። በድርቁ ሳቢያ ከ2 ሚሊዮን በላይ የቤት እንስሳት አደጋ እንደተደቀነባቸው የገለጸው ድርጀቱ፣ እስከ መጪው ሚያዚያ ድረስ ዝናብ ካልዘነበ ጉዳቱ የከፋ ይሆናል ብሎአል።