ጸሃፊ በፈቃዱ ሃይሉ ታሰረ

ኅዳር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- የተለያዩ ፖለቲካዊ ትችቶችንና መረጃዎችን በመጻፍ የሚታወቀው በፈቃዱ ሃይሉ ህዳር 02/2009 ዓም “ኮማንድ ፖስቱ ሊያናግርህ ይፈልጋሀል” ተብሎ  በፖሊስ ተጠርቶ  በድጋሜ ለእስር ተደርጓል።

በ2006 ዓም ዞን ዘጠኝ እየተባሉ ከሚጠሩ ጻሃፊዎች ጋር ታስሮ ከ18 ወራት የእስር ጊዜ በሁዋላ በ20 ሺ ብር ዋስ የተፈታው በፈቃዱ ፣ ከእስር ከወጣ በሁዋላ ውይይት መጽሄት ላይ በዋና አዘጋጅነት የስራ ነበር። አቃቢ ህግ ቀደም ብሎ ይግባኝ የጠየቀበት ክስ ህዳር 6/2009 ዓም ውሳኔ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል።